DISTRICT UNION PROFILE
About Sodo District Union
የወላይታ ሶዶ ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ህብረት ጽ/ቤት በወላይታ ቀጣና ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ 20 ህብረቶች አንዱ ሲሆን የተቋቋመው በ2010 ዓ.ም ነው።
በተለያዩ አከባቢዎች በቁጥር በርከት ያሉ አጥቢያዎች በመኖራቸው ህብረት ለማድረግ እና አስተዳደራዊ መዋቅሮችን በመዘርጋት አገልግሎቶች የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እና አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን በህብረት ለመፍታት የሚያግዝ የአሰራር ስርዓት ያለው የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ነው።
የተቋቋመውም አላማ በቀዳሚነት ወንጌል ማዳረስ እና ደቀ መዛሙርትን ማፍራት ነው። ወንጌልን ተደራሽ በማድረግ ረገድ በአጠቃላይ ከ83 በላይ ሚሲዮናውያንን ያቀፈ ሲሆን ከነዚህም 3ቱ አለም አቀፍ ወይም ድምበር ዘለል ሚሲዮናውያን ናቸው።
ደቀመዛሙርት ለማፍራት በቤተክርስቲያኒቱ በተቀመጡ የስልጠና መንገዶች በማሰልጠን መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ ስልጠናዎችን በመስጠት ምዕመናንን የማብቃት ስራ የሚሰራበት ጽ/ቤት ነው።
በመደበኛ ስልጠናዎች በእቅድ መሠረት በተቀመጡ ጊዜያት የሚደረግ ሲሆን መደበኛ ያልሆነው ወቅቱን ተንተርሶ የሚፈጠሩ የስህትት አስተምህሮ እና ልዩ ልዩ ፀብ ጫሪ የሆኑ ፍንጮች ሲስተዋሉ የሚዘጋጅ ስልጠና ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን በአስቸኳይ ተደራሽ ያደርጋል።
በሁሉም ዘርፎች የመንፈሳዊ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት በልጆች ዘርፍ ለሠንበት ተማሪ እና ለመምህራኖቻቸው የሚሆኑ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ በማድረግ ፤ የወጣቶች ዘርፍ አገልግሎቶች ላይ የወንጌል ፌስቲቫሎችን በማዘጋጀት ፤ በሴቶች ዘርፍም እንዲሁ የራሱ ወንጌላዊ ተመድቦለት ስልጠናዎችን የሚያገኙበት ፣ ወደ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትም ተደረሽ የሚሆንበትን እና የሚሠራጭበት መንገድ በመኖሩ ደቀመዛሙርትን የማባቃት ስራ በለፋ የወንጌል ስራን ሊያፋጥን ችሏል።
በህብረቱ ከሚሰጡ አገልግሎቶች አንዱ በጎ አድራጎት ስራ ላይ በመሰማራት የእግዚአብሔርን ፍቅር ማካፈል ነው። በህብረቱ የሚገኘው ገንዘብ ሁሉም በጌታ ስም የተሰበሰበ እንደመሆኑ ለታቀደለት አላማ እንዲውል ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ማስተዋል የተሞላበት የአሰራር ሂደት ተከትሎ የሚሰራ ነው።
ለበጎ አድራጎት አላማ ይሆን ዘንድ ዶርቃ የበጎ አድራጎት ብድን እንዲቋቋም በማድረግ በአነስተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ አቅመ ደካሞች ፣ ወላጅ አልባ ህፃናት ፣ የታመሙ (ለህክምና ከፍተኛ ወጪ የተጠየቁ) እና በተለያዩ አጋጣሚዎች ችግሮች የገጠሟቸው ሰዎች ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው በመምጣት ድጋፎችን የሚጠይቁ አካላትን የማስተባበር እና የህብረቱ አቅም በሚፈቅደው ልክ የተለያዩ የአሰራር ሂደቶችን ተከትሎ የሚያግዝበት ፤ በቀጣይነት መታገዝ የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት እና ስልጠና መርሐግብር ውስጥ በማካተት ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ የመፍጠር ስራ ይሰራል እንዲሁም ከቀጣናው የሚሰጡ ረዘም ላለ ጊዜ በአገልግሎት የቆዩ እና በሽምግልና እድሜ ላይ የሚገኙ አገልጋዮችን በቋሚነት ይደግፋል።
በዓላት ሲደርሱ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት ስራ በመስራት ማህበራዊ ትስስርን በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ በማድረግ መንፈሳዊ አንድነትን ይጠብቃል።
የሶዶ ህብረት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሲገኝ በውስጡም 50 አጥቢያ ቤተክርስቲያን በማያያዝ የወንጌል አገልግሎት በማገልገል ላይ ይገኛል።

OUR LOCATION
Wolaita Sodo
ወልድ ያለው ሕይወት አለው